የደ/ማርቆስ ከተማ አስተዳደር በአማራ ብሄራዊ ክልላዊ መንግስት የምትገኝ የዞን ዋና ከተማ ነች፡፡ ደብረማርቆስ ከተማ በ4845 ዓም በጎጃሙ ገዠ ደጅ አዝማች ተድላ ጓሉ የተቆረቆረች ሲሆን መንቆረር የሰው ስም መጠሪያ ነበር፡፡በጥንት ዘመን ከተማዋን በርዕስትነት ያስተዳድሯት ከነበሩት  ከሁለቱ የሳሮን ልጆች ዝናና መንቆረር መካከል የአንደኛው ልጅ ስም ነበር። ይህንንም ስም መጠሪያ አድርጋ አመታትን አሳልፋለች።  በ1939 ዓ.ም ተወልደው በ18 93 ዓ.ም  ያረፉት ን/ተክለሃይማኖት በ1872 ዓ.ም ከነገሱ ከሁለት አመታት በኋላ በ1874 ዓ.ም የመርቆርዮስ ቤተክርስቲያን በመብረቅ ተመትቶ በመቃጠሉ ምክንያት መልዕልተ አድባር ቅዱስ ማርቆስ ቤተክርስቲያንን በማሰረታቸው ከተማዋ ደብረ ማርቆስ ተብላ እንድትጠራ  አዋጅ በማስነገራቸው ደብረ ማርቆስ ተብላ መጠራት ጀመረች፡፡

ደ/ማርቆስ ከተማ በአንድ ከንቲባና  በ14 በሚደርሱ ትንንሽ የተያዩ ስያሜ የተሰጣቸው ሰፈሮች የነበሯት መሆኑን መረጃዎች ይጠቁማሉ።

እነርሱም፡- 

  • ካህን ሰፈር፡- ከቅዱስ ማርቆስ ቤተክርስቲያን እስከ ደብረ ማርቆስ ሪፈራል ሆስፒታል
  • ፈረስ ቤት፡- ቅዱስ ሚካኤለል ቤተክርሲቲያን እስከ ንጉስ ተክለሃይማኖት ት/ቤት
  • ቅሬ ሰፈር፡- የአሁኑ ቀበሌ 06 አካባቢ
  • ነጋሪት መቺ ሰፈር፡- ከቅዳምን ገበያ አንስቶ እስከ አብማ ት/ቤት
  • ሰፊ ሰፈር፡- ከንጉስ ተ/ሃይማኖት ት/ቤት እስከ ውትርን ወንዝ
  • ካህን ሰፈር፡- ከማርቆስ ቤተክርሲቲያን እስከ ስንዴጎም ጸበል
  • አውራ በር፡-   መሃል አደባባይ አካባቢ
  • ደመራ ሰፈር፡-   አብማ ቤተክርስቲያን ፊትለፊት
  • ማክሰኝት ሃይሉ ገበያ፡- እንድማጣ ቤተክርስቲያን እስከ አውሮፕላን ማረፊያ
  • ቅዳምን፡- ቀበሌ 02 ጽ/ቤት ጀምሮ እስከ መሃል ገበያ ያለው
  • ግምጃ ቤት፡- ከደብረ ማርቆስ ሆስፒታል እስከ ኪዳነምህረት ቤተክርስቲያን
  • ባሶ በር፡- ከታቦቱ መውረጃ ጀምሮ እስከ ቀበሌ 02 ጽ/ቤት ያለው
  • አብማ፡- ከአብማ ማርያም  ቤተክርስቲያን እስከ መሰናዶ 2ኛ ደረጃ ት/ቤት
  • ድብዛ ፡-ከአብማ ማርያም ቤተክርስቲያን እስከ መሰናዶ 2ኛ ደረጃ ት/ቤት

ስትቆረቆር 272 ሄ/ር የሚገመት ስፋት የነበራት ደብረ ማርቆስ  ከተማዋ ከባህር ወለል በላይ በአማካይ ከ2420- 2550 ሜትር ከፍታ ሲኖራት ለኑሮ ተስማሚ የሆነ ወይና ደጋ  የአየር ንብረት ያላት ጥንታዊ ከተማ ናት። ደብረ ማርቆስ የጎጃም ጠቅላይ ግዛት ዋና ከተማ   በመሆን ለረዥ  ዘመናት አገልግላለች። 

ከተማዋ ከክልሉ ርዕሰ መዲና  ባህርዳር ከተማ 265 ኪ.ሜ ከአዲስ አበባ ደግሞ በ299 ኪ.ሜ ርቀት ላይ ትገኛለች፡፡ ከተማዋ በምስራቅ አነደድ፣ በምዕራብ ፣በሰሜንና በደቡብ ጎዛመን ወረዳ ያዋስኗታል፡፡ ደጋና ወይና ደጋ የአየር ንብረት ያላት ስትሆን ትርፍ አማራች ከሚባሉ ከተሞች አንዷ ናት። 

  • የሙቀት መጠኗ ከ18-20ድግሪ ሴሊሽየስ ሲሆን አመታዊ የዝናብ መጠኗም ከ100-1300 ሚ.ሜ ይደርሳል ተብሎ ይገመታል።

የደ/ማርቆስ የቆዳ ስፋት  29275 ሄ/ር ሲሆን   ብረ ማርቆስ ከተማ ሜትሮፖሊታን የሆነችው በ2013 ዓ.ም  ሲሆን በ4 ክፍለ ከተማና በ14 የከተማና 6 የገጠር ቀበሌዎች በድምሩ በ20 ቀበሌዎች ተዋቅራለች።